ጠቅላላ

General

ዓለምን ዞሬ አየሁት

Lyrics

ዓለምን ዞሬ አየሁት ሁሉን በተራ ቀመስኩት

ፈጽሞ የለም /2/ ሠላም አንደ ልጅሽ ቤት

ሀብት ንብረቴን ጨረስኩና

ጉልበቴ ሁሉ ደከመና

ጎስቋላ ሆንኩኝ /2/ ደካማ የሌለው ጤና

ስቃ አሳስቃ ተቀብላ

መልኳን አስውባ ተኳኩላ

ዛሬ ጣለችኝ /2/ ይህች ዓለም አትረባም ብላ

የትላንትና ወዳጆቼ

ዛሬ ሲሆኑ ጠላቶቼ

ባክኜ ቀረሁ /2/ በዓለም ላይ ተንከራትቼ

የአባቴ ቤት ሲናፍቀኝ

ፍቅሩ ምህረቱ ትዝ ሲለኝ

ጎስቋላው ልጅህ ደካማው ልጅህ ጌታ ሆይ ዛሬ መጣሁኝ

እናቴ አንቺን ንቄ ትቼ

የአባቴን ቤት እረስቼ

ተሰቃየሁኝ ተንከራተትኩኝ ልደሰት በዓለም ገብቼ

አባቴ ሲያየኝ ተደስቶ

ጎረቤቶቹን ሁሉ ጠርቶ

ሰርጉን ደገሰ /2/ የበደልኩትን እረስቶ

እስከ አሁን ድረስ በድያለሁ

ዓለም ደህና ሁኚ አብቅቻለሁ

ወደ አባቴ ቤት /2/ ዳግመኛ ተመልሻለሁ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening