ጠቅላላ

General

ያልጠፋነው

Lyrics

ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር ምህረት የተነሳ ነው

ቸርነቱ ከቶ አያልቅምና ርህራሄው ከቶ አያልቅምና

ይገባዋል ክብርና ምስጋና

ፈታኝ ሲያንገላታን በባህር ስንሔድ

ማዕበል ተነስቶ ያ የሥጋ ሞገድ

ሕይወት ስትመዝን ልባችን ሲናወጥ

ለጠላት ሳይሰጠን አደረገልን ጸጥ

ስለሆነ ርህሩህ ፈጥኖ የማይቀየም

ለንስሀ እንቅረብ አንሂድ ወደ ዓለም

ምስክር ነን እኛ አይተናል ማዳኑን

በእርሱ ተማርከናል ቀምሰን ቸርነቱን

በበደልነው በደል ማረን እንላለን

ከአንተ ተለይተን ወዴት እንሄዳለን

ዓለም የማያውቀው የማይመረምረው

በውስጣችን አለ እኛ እምናመልከው

ከእንግዲህ አልፈልግም የሸንጋይ ምላስ

ቃልህ ይቆጣጠረኝ በስጋም በነፍስ

አንተ ካከበርከኝ ማን ያዋርደኛል

ዓይኔን ከሰው አንሳው አሁንስ በቅቶኛል

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening