ጠቅላላ

General

እያለፈ ነው ዘመኔ

Lyrics

እያለፈ ነው ዘመኔ ትዕዛዙን ሳልፈፅም ወየው ለእኔ /2/

በጠራኝ ጊዜ ምን እላለሁ ና ብሎ ወደ እኔ /2/

በወጣትነቴ ሳልሰራ እያየሁ አለፈኝ ብዙ አዝመራ /2/

ከእንግዲህ በመስራት ጌታ ሆይ ልኑር ከአንተ ጋራ /2/

የማስብበት በየዕለቱ ንጹህ ልብ ስጠኝ አቤቱ /2/

ከትዕዛዝህ ውጪ በመሆን እንዳልቀር በከንቱ /2/

እንደየስራው ለመክፈል በግርማ መንግስቱ ሲመጣ /2/

ማን ይሆን የሚቆም ከፊቱ ፈተናን የወጣ /2/

እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ እየተማራችሁ ከቃሉ /2/

ይመጣሉና በእርሱ ስም አምላክ ነን የሚሉ /2/

ትዕግስትን በመያዝ ሁላችሁ እስከመጨረሻው ጠንክሩ/2/

ያን ጊዜ ይሆናል በእርሱ ዘንድ የማዳን ተግባሩ /2/

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening