✦
ጠቅላላ
•General
ዘጠኝ ሰዓት ሲሆን
Lyrics
ዘጠኝ ሰዓት ሲሆን አባት ሆይ በመስቀል ላይ ሆነህ አባት ሆይ
ድምጽህን በማሰማት አባት ሆይ ነፍስህን ሰጠህ አባት ሆይ
የሰማይ ከዋክብት በሙሉ ረገፉ
ጨረቃና ፀሐይ ደምን አጎረፉ
ብርሃናት ጨለሙ ጠፍተው ተለያዩ
ስጋህን በመስቀል ተገልጦ ስላዩ
ጌታችን ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሳለ
አሰምቶ ጮኸ ተጠማሁ እያለ
ማርና ወተት ለሚመግበው
ሐሞት አመጡለት ይቅመሰው ብለው
አካሉ ሲወጋ ውሃ ደም ፈሰሰ
በምድር ተረጭቶ ዓለምን ቀደሰ
የእስራኤል ሴቶች ዋይ ዋይ ሲሉልህ
ለእነርሱ አዘንክ እንጂ ለአንተስ አላሰብክ
እናትህ ስታለቅስ በመስቀል ስር ሆና
ዮሐንስን ሰጠህ ጠብቆ እንዲያጽናና
መላዕክትም ታዩ አጋንንትም ሸሹ
የአይሁድ ሰራዊት ፈርተው ተረበሹ
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.