✦
ጠቅላላ
•General
የጸጸት እሮሮ
Lyrics
አምላክ ሆይ ወደ እኛ ባትመጣ /2/
ለብሰህ የማርያምን ስጋ /2/
ባክኖ የነበረው የአዳም ዘር /2/
ውጤቱ ነበር የሚያሰጋ /2/
በዚያ ዓመት በዚያች ወር በዚያች ቀን /2/
ድህነትን ለሰው ልጅ ስትሰጥ /2/
ምን የበዛ ነበር ትህትና /2/
ትዕግስትህ የማይለወጥ /2/
የአሾህ አክሊል ደፍተህ /2/
በራስህ ጎንህን ሲወጉ በጦር /2/
አንተ ግን ለእነርሱ ከአባትህ /2/
ምህረትን ትለምን ነበር /2/
ግን መቼ አወቁህ እነርሱ /2/
በሃጢያት ደንድኖ ልባቸው /2/
መድሃኒታቸውን ገረፉት ሰቀሉት /2/
አንተም ሞትክላቸው /2/
በዚያች በደብረ ዘይት ቦታ /2/
ደስታና ለቅሶ ሲፈልቅ /2/
ከቶ ከየት ይሆን እጣዬ /2/
ያን ጊዜ የእኔ አወዳደቅ /2/
የጸጸት እሮሮ በፊትህ /2/
እንዳያቃጥለኝ እኔን /2/
እርዳኝ ፈጣሪዬ እኔን /2/
አድሰው የዛገው ልቤን /2/
ዳግም ስትመጣ ለፍርድ /2/
ከዓለም ፍፃሜ በኃላ /2/
ኸረ እንዴት እድለኞች ናቸው /2/
በፊትህ የሚያገኙት ተድላ /2/
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.