ጠቅላላ

General

የት ይሆን መግቢያዬ

Lyrics

በስራዬ የት ይሆን መግቢያዬ /4/

ጨነቀኝ ጠበበኝ ነፍሴ ወዲያልኝ /2/

ተሸክሜ የሃጢያት ክምር /2/

ይመሻል ይነጋል በከንቱ ስዞር /2/

ገሰገሰ ቀኑ ጨለመብኝ /2/

ዋ ለነፍሴ ምንም ስንቅ አልያዝኩኝ /2/

በድያለሁ ወደ አንተ እጮሀለሁ /4/

ይቅር በለኝ እማጸንሀለሁ

ችላ አትበለኝ ከፊትህ ቆሜአለሁ

አለፈብኝ በከንቱ ጊዜዬ /2/

እየጓጓሁ ለዚች ለስጋዬ /2/

በንስሀ ሳላጥበው እድፌን /2/

ልትደርስ ነው ያች የፈተና ቀን /2/

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening