✦
ጠቅላላ
•General
ወደ ምስራቅ እዩ
Lyrics
ወደ ምስራቅ እዩ ወደ ፀሐይ መውጫ
ድንግልን ክበቧት እንበል ሃሌ ሉያ
ለአምላክ እናት ለአዛኝት
እልል እንበል እንዘምርላት
ወገኖች ተነሱ እናታችን መጣች
ስሟን ስንጠራ መቼ ትቀራለች
የተከዘን ልታጽናና
ነይ ስንላት ትመጣለችና
የጽጌው ማህሌት መዝሙር ሲጀመር
ማርያም ትመጣለች በደመና በአየር
ንኢ ስንል በሰዓታት
እሷ አትቀርም ትመጣለች በእውነት
ፍልሰታ ሲጀመር ቃል ኪዳን ገብታለች
የሌሊት ውዳሴን ንኢን ትሰማለች
ህፃናቱን በበረከት
ልትጎበኝ ትመጣለች በእውነት
በፍጹም ቸርነት እንዲምረን ጌታ
በአማላጅነትሽ ሁኝልን መከታ
እናታችን አለኝታችን
እንድናለን ድንግል አንቺን ይዘን
ሃሌ ሃሌ ሉያ /4/ እስመ ዝንቱ ኡራኤል
እስመ ዝንቱ ለዓለም ብርሃን
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.