✦
ጠቅላላ
•General
አትተወኝ አትጣለኝ
Lyrics
አትተወኝ አትጣለኝ /2/
ወድቂያለሁ እና ጌታ ሆይ አንሳኝ /2/
ቸሩ መድሃኒቴ የአልአዛር ቤት ራት
የኑሮዬ ጣዕም የሕይወቴ መብራት
በሃጢያት ጭቃ ላይ ወድቂያለሁና
ጌታዬ ሆይ አንሳኝ እጅህን ዘርጋና /2/
የሰጠኸኝ ክብር የልጅነት ስልጣን
እንደ ሶምሶን ሲወድቅ ከደሊላ ጋር
እርቃኔን ቀረሁኝ ተላልፌ ሕግህን
አምላኬ ዘርጋልኝ የምህረት እጅህን
ጌታዬ ዘርጋልኝ የምህረት እጅህን
ዘወትር እየበደልኩ ከህግህ እርቄ
በሃጢያት ጭቃ ላይ ክፉኛ ወድቄ
በበደል እስራት ተይዣለሁና
አባቴ ሆይ ማረኝ መሀሪ ነህና
ጌታዬ ሆይ ማረኝ መሀሪ ነህና
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.