✦
ጠቅላላ
•General
እመቤቴ የአምላክ እናት
Lyrics
እመቤቴ የአምላክ እናት
ላመስግንሽ ቀን ከሌሊት
ለልጅሽም ክብር ውዳሴ
ታቀርባለች ዘውትር ነፍሴ /2/
ልቤ ተነሣሣ ተቀኘ ለክብርሽ
በፍፁም ትህትና ሊያመሰግንሽ
ጽዮን መጠጊያ ነሽ የአብርሃም ድንኳን
የታጠረች ተክል እመብርሃን
የለመለመች መስክ አምላክ የመረጣት
የጽላቱ ኪዳን ታቦቱ ድንግል ናት
የሰማይ የምድር ንግስት ናትና
ክብር ይገባታል ዘውትር ጠዋት ማታ
አደራሽን ማርያም የሁሉ እናት
በምልጃሽ አስቢኝ ኃላ ስራቆት
ያንን የእሳት ባህር አሻግሪኝ ድንግል ሆይ
እንዳልወድቅ እንዳሞት ከቶ እንዳላይ ስቃይ
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.