✦
ጠቅላላ
•General
ተክለሐይማኖት ፀሐይ
Lyrics
ተክለሐይማኖት ፀሐይ የኢትዮጵያ ሲሳይ
ምዕራፈ ቅዱሳን /2/ በነፍስም በሥጋ አትርሳን
የቅዱሳን እርስት የኢትዮጵያው ብርሃን
የጸሎት ባለቤት የነዳያን መድህን
ገና ሳትወለድ አምላክ የመረጠህ
የድውያን ህመም ፈዋሹ አንተ ነህ /2/
ገና በሶስት ቀን በህፃንነትህ
ጌታን አወደሰው ቅዱስ አንደበትህ
ቀድሞም እግዚአብሔር አስቦሃልና
በወጣትነትህ ወጣህ ለምነና /2/
ሌትና ቀን ሳትመርጥ ክረምትና በጋ
ስትፀልይ ውለህ ስትፀልይ አነጋህ
በመቆምህ ምክንያት አንድ እግርህ ቢነሳ
ጸሎትህን ፈጸምክ ለስጋህ ሳትሳሳ /2/
ምንኛ ድንቅ ነው ቅዱስ ያንተ ብርታት
ሰባት ዓመት ሙሉ በአንድ እግርህ ጸሎት
የዓለም ግሳንግሱ ሀብቱ ሳይስብህ
ለኢትዮጵያ ፀለይክ ቆመህ በአንድ እግርህ /2/
የሐይማኖት ተክል የኢትዮጵያ አባት
ምህረትን ከአምላክህ ለሀገርህ አሰጣት
እኛንም አግዘን ጽድቅን እንድንሰራ
በተሰጠህ ስልጣን ጠብቀን አደራ /2/
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.