ጠቅላላ

General

ያሬድ ካህኑ

Lyrics

ያሬድ ካህኑ ዘመረ /2/

ዘመረ ያሬድ ዘመረ አምላኩን አመሰገነ /2/

አርያም በማለት ያሬድ ዘመረ

ማህሌት ጀመረ ያሬድ ዘመረ

ዜማውን ከመላዕክት እያስተባበረ

ምስጋና አቀረበ ያሬድ ዘመረ

በዜማ መሣሪያ ያሬድ ዘመረ

ጸናጽል አነሳ ከበሮ መቋሚያ

በግዕዝ ዕዝ በዕዝል ያሬድ ዘመረ

በአራሪ ራይ ዜማ ያሬድ ዘመረ

ከብሉይ ከሐዲስ ምስጢር እያስማማ

በዜማው ምልክት ያሬድ ዘመረ

የአምላክን መከራ ያሬድ ዘመረ

የመስቀሉን ነገር የማዳኑን ስራ

ደሙ እየፈሰሰ ያሬድ ዘመረ

በጦር ተወግቶ ያሬድ ዘመረ

ሊቁ ማህሌታይ በመንፈስ ተቃኝቶ

በጥኡም ልሳኑ ያሬድ ዘመረ

በተሰጠው ጸጋ ያሬድ ዘመረ

ለንጉስ እግዚአብሔር ለአልፋ ኦሜጋ

ድጓ ጾመ ድጓ ያሬድ ዘመረ

ምዕራፍ መዋሲት ያሬድ ዘመረ

ምስጢር ተገልጾለት ከሰማይ መላዕክት

የዜማ መሠረት ያሬድ ዘመረ

ፈልፈለ ዝማሬ ያሬድ ዘመረ

የኢትዮጵያ ኩራት የተዋህዶ ፍሬ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening