✦
ጠቅላላ
•General
እጹብ ድንቅ ነው
Lyrics
እጹብ ድንቅ ነው ውለታው
እግዚአብሔር ለኛ ያረገው
ከቶ አይጥለንም ለዘለዓለም
እንደ አምላካችን ማንም የለም
ወድቀን ነበረ ተነስተናል
ባህር አሻግሮ አቁሞናል
ድንቅ አደረገ ታምር ሰራ
እያንሳፈፈ ያን ተራራ
የጠፋውን በግ የፈለገ
እራሱን ባዶ አደረገ
መስቀል ታቅፎ ክንዱ ዛለ
ምን ያልሆነልን ነገር አለ
ከአባትም በላይ አባት ነው
የልጆቹ እንባ የሚገደው
የጭንቀታችን ተካፋይ
አዛኝ ጌታ ነው ሁሉን ቻይ
ዳግም እንድንቆም በሕይወት
ጨክኖ ወደደን እስከሞት
ከእንግዲህ አንፈራም እንጸናለን
ለክፉ የማይሰጥ አባት አለን
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.