ጠቅላላ

General

የስላሴን መንበር

Lyrics

የስላሴን መንበር ቅዱሳን ከበውት

ኪሩቤል በደመና ዙፋኑን ይዘውት

ድንግልን ከመሃል ሚካኤልን ከፊት

አእላፍ መላዕክት ሲሰግዱ በፍርሃት

እዩ ተመልከቱ የሰማዩን ድምቀት

እዩ ተመልከቱ የሰማዩን አባት

የስላሴን መንበር ቅዱሳን ከበውት

እያሸበሸቡ የሰማይ መላዕክት

ካህናተ ሰማይ ስሉስ ቅዱስ ሲሉ

በጽድቅ ስራቸው በምድር ይታያሉ /2/

የቅዱሳን ህብረት የቅዱሳን ሀገር

ሲያወድስ ይኖራል የስላሴን መንበር

ፍቅርና ርህራሄን የተሞላች ሰማይ

እግዚአብሔር ያድለን በትንሣኤ እንድናይ /3/

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening