✦
ጠቅላላ
•General
ዝም አትበሉ
Lyrics
ዝም አትበሉ እግዚአብሔርን አመስግኑ /2/
ቅዱስ /3/ ስሉስ ቅዱስ በሉ
መላዕክቱ ሁሉ ምስጋናን ጀምሩ
ቅዱስ ቅዱስ በሉ
የሙሴ እህት ማርያም ከበሮውን አንሽው
በምስጋና መዝሙር እስራኤልን ጥሪው
አምላክን እናክብር እንዘምር በእልልታ
ከእኛ ጋር ይሆናል የሠራዊት ጌታ /2/
ፍጥረታትም ጩኹ ሰማያት ዘምሩ
ስለ ቅድስናው ውዳሴ ጀምሩ
ዳዊት ሆይ ተነሣ ስለ ጽዮን ዘምር
ከበሮው ይመታ በገናው ይደርደር /2/
ወገኖች እንዘምር ለእግዚአብሔር ክብር
ውለታው ብዙ ነው ለእኛ ያለው ፍቅር
ማዳኑን ያያችሁ ዘምሩ በእልልታ
ለጌታ ለእግዚአብሔር ለሠራዊት ጌታ /2/
ባህሩን አቋርጦ ወንዝ ያሻገራችሁ
ተራራውን ንዶ ያቀለለላችሁ
በአውሎ ነፋስ መሐል መንገድ ላለው ጌታ
ለንጉስ ክርስቶስ እንዘምር በእልልታ /2/
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.