✦
ጠቅላላ
•General
ጠላቴን ጌታዬ
Lyrics
ጠላቴን ጌታዬ አንበረከከልኝ
እጅግ ተዋረደ በጣሙን ደስ አለኝ
ለዚህ ድንቅ ውለታህ ምን ልክፈልህ ጌታ
ስለ ለወጥክልኝ ሀዘኔን በደስታ
እግዚአብሔር ብርሃኔ መድሃኒቴ ነው
የሚያስደነግጠኝ የሚያስፈራኝ ማነው
አስጨናቂዎቼ በከበቡኝ ጊዜ
ፈጥኖ ደረሰልኝ ሳለሁ በትካዜ /2/
ይቅርታህ በአይኔ በፊቴ ነውና
ሃጢያቴ ቢበዛም አልተውከኝምና
እግዚአብሔር የሕይወቴ መሸሸጊያዬ ነው
በእርሱም ትመካለች እድል ፈንታዋ ነው /2/
ነፍሴን ሀዘን ከቧት እጅጉን ተጨነቃ
ስትጮህ ወደ አንተ ምህረትህን ናፍቃ
እራርተህ ፈወስካት አነሳሃት ጌታ
መቼም አይረሳም የአንተ ውለታ /2/
አጥንቶቼ ደክመው በለቅሶ በዋይታ
አይኔም በሀዘኔ በእንባ ተሞልታ
ልቤ ታውኮብኝ ሰላሜ ደፍርሶ
አዳነኝ ጌታዬ በምህረቱ ዳሶ /2/
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.