ጠቅላላ

General

በገና አንስተን

Lyrics

በገና አንስተን መሰንቆን

እናመስግነው ስምህን

እንደ አምላካችን ማንም የለም /2/

ይክበር ይመስገን ለዘለዓለም /2/

ዓለም ሞኝነት ይመስለዋል

ለአንተ መንበርከክ ይከብደዋል

ፍቅርህን ቀምሰን ዝም አንልም /2/

እንዘምራለን ለዘለዓለም /2/

ሞኝነት ለኔ መች ሆነና

ፊትህ ያቆመኝ ለምስጋና

እንድቀኝልህ ግድ የሚለኝ /2/

ፍቅርህ ብቻ ነው የማረከኝ /2/

ፈውስን ስትሰጠን ስትባርከን

ፍቅርህን ልከህ ስትጎበኘን

ጉልበት ይጸናል ባንተ ጸጋ /2/

ማነው የሚከፍለው የአንተን ዋጋ /2/

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening