✦
ጠቅላላ
•General
ለማርያም እንዘምራለን
Lyrics
ለማርያም /2/ እንዘምራለን ለዘለዓለም /2/
ለዘለዓለም ህዝቅኤል ብሏል ለዘለዓለም
የተዘጋጅ በር ንጽህይት ናት በእውነት
በፍፁም ድንግል አብነት አድርገን
እኛም እርሱን በፍፁም ፍቅር እንዘምራለን /2/
የዋህት እርግብ ለዘለዓለም ሠላም አብሳሪ ለዘለዓለም
ጨለማ ሕይወቴን ብርሃንን አብሪ
እማጸንሻለሁ ድንግል ለነፍሴ
አደራ ቅድስት አንቺ ነሽ ዋሴ /2/
እጅግ የበዛ ነው ለዘለዓለም ያለኝ ፍቅር አይወሰንም
አይነገርም በእርሷ ደስ ይለኛል ሐሴት አደርጋለሁ
ስሟን እየጠራሁ እዘምራለሁ /2/
ለዘለዓለም ንኢ ንኢ ስላት ለዘለዓለም ቀንና ሌሊት
አትለየኝም ለእኔስ ቅርቤ ናት
እጹብ እጹብ ብለው አመሰገኗት
ክብርዋን ሊገልጹ ቢያጥራቸው ቃላት /2/
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.