ጠቅላላ

General

ወይቤሎሙ ሐሩ

Lyrics

ወይቤሎሙ ሐሩ ወመሐሩ ለዘየአምን /2/

ወንጌለ መንግስተ ሰማያት /4/

በሕይወታችሁ ስበኩ በኑሮአችሁ

ከጽንፍ እስከ ጽንፍ በዓለም ዙሪያ አዳርሱ ሳትሰለቹ

ደመና ጠቅሳችሁ እንደወፍ

ወንጌለ መንግስተ ሰማያት /2/

በሃጢያት ገመድ ተይዞ ለታሰረው

በዓለም ጽልመት ለተዋጠው

የእውነቱ መንገድ ብርሃኑ ለጠፋበት

በሁለንተናው ፈንጥቁበት

ወንጌለ መንግስተ ሰማያት /2/

የጽድቅ እንጀራ በማጣት ለተራበው

የሕይወትን ውሃ ለተጠማው

ቀቢጸ ተስፋ በልቡ ላደረበት

የወንጌልን ማዕድ አቅርቡለት

ወንጌለ መንግስተ ሰማያት /2/

አይንተ ወንጌል ካህናት ሊቃውንት

ለተልዕኮ የጠራችሁ

ከእውነተኛው ምንጭ ከጌታ ከባህሩ

የሕይወትን ውሃ የጠጣችሁ

ወንጌለ መንግስተ ሰማያት /2/

ሁለንተናችሁ ይነበብ ፊደል ይሁን

በትዕዛዙ ሔዳችሁ

ስራችሁ ይብራ በዓለም እንደ ሻማ

በሕይወታችሁ ሰብካችሁ

ወንጌለ መንግስተ ሰማያት /2/

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening