✦
ጠቅላላ
•General
እርግብየ
Lyrics
እርግብ /2/ ማርያም እሙ ለእግዚእየ
በቀለመ ወርቅ ጻአፊ ስምየ
በአምደ ብርሃን ጻአፊ ስምየ
በቀለመ ወርቅ ጻአፊ ስምየ
የተመረጥሽ ጌጤ ፈርጤ ሽልማቴ
የክብሬ አክሊል ነሽ ለኔ እመቤቴ እርግብየ
ወደ አንቺ እጮሃለሁ በችግሬ ጊዜ
እንድታርቂልኝ የልቤን ትካዜ እርግብየ
የማትፈርሺ መቅደስ ንጽህት አዳራሽ
የመለኮት እሳት በማህጸንሽ የያዝሽ እርግብየ
የድህነቴ ምክንያት የሕይወቴ ፋና
የችግሬ ደራሽ ርህርህተ ህሊና እርግብየ
ስጠራ ስምሽን ከጠዋት እስከ ማታ
ፈጥነሽ ድረሺልኝ እንዳልንገላታ እርግብየ
የነቢያት ትንቢት የሰማዕታት አክሊል
ምዕረገ ጸሎት የወርቅ መሰላል
ምርኩዝ መደገፊያ የሐይማኖት በትር
ሆነሽ የተገኘሽ የሕይወት ማህደር እርግብየ
መንገዴ ጨልሞ ወድቄ እንዳልቀር
ደግፈሽ አሻግሪኝ ያን የሃጢያት ባህር እርግብየ
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.