✦
ጠቅላላ
•General
ስምሽን ጠርቼ
Lyrics
ስምሽን ጠርቼ መቼ አፍራለሁ
ማርያም ብዬ መቼ እወድቃለሁ
የምጽናናበት ስምሽ ነውና
ድንግል ሆይ ላቅርብ ላንቺ ምስጋና
ጨለማ ውጦኝ በጠላት ሀገር
ለዘመናትም ስረገጥ ስኖር
ዲያብሎስ ማርኮ ሲያሰቃየኝ
የዓለሙን መድን ወለድሽልኝ
ከአባቶቼ ርስት ከሀገር ወጥቼ
በአህዛብ ሀገር ስኖር ተሽጬ
ደርሰሽ አጽናንተሽ አከበርሽኝ
ብቸኝነቴን አስረሳሽኝ
ድንኳኑ ሞልቶ ሰዉ ታድሞ
አስተናባሪው በጭንቀት ቆሞ
ምን አቀርባለሁ ብዬ ስቸገር
ምልጃሽ ደርሶልኝ ዳንኩኝ ከማፈር
ያሰብኩት ሀሳብ ደመና ሆኖ
ቢበተንብኝ እንደ ጉም ተኖ
ይሆናል ያልኩት ሳይሆን ቢቀርም
በእመ አምላክ እኔስ ተስፋ አልቆርጥም
እናት አባቴ ባያስታውሱኝ
ይህቺ ዓለም ንቃ ገፍታ ብትተወኝ
አንቺ ካለሽኝ ምን እሆናለሁ
አውሎ ነፋሱን ባህሩን አልፋለሁ
ጠላቴ ደርሶ ቢያንገላታኝም
መከራ አብዝቶ ቢያስጨንቀኝም
አላቋርጥም ያንቺን ምስጋና
ውለታሽ ድንግል አለብኝና
ክፉዎች ደርሰው ቢዝቱብኝም
አንቺን መውደዴን አያስተዉኝም
በአህዛብ መሃል ስምሽን ስጠራ
መከታ ሁኚኝ እናቴ አደራ
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.