✦
ጠቅላላ
•General
አንቺን የያዘ ሰው
Lyrics
አንቺን የያዘ ሰው ምን ይጎድልበታል
በምልጃሽ በረከት ቤቱ ሞልቶለታል
ዘር መከር ባይኖረው ጎተራው ባይሞላ
ሁሉም ይሸፈናል በረድኤትሽ ጥላ /2/
በረከትሽ ብዙ የደናግል ገንዘብ
የምስኪናን እናት የርሁባን ቀለብ
ለሁሉ መጋቢ ጸጋሽ የማይጎድል
ስምሽ ጥዑም ምግብ ከረሃብ የሚያስጥል /2/
አንቺ ብትመጪ ከምስኪኗ ቤቴ
እንደ መጥምቁ እናት በዛልኝ ሐሴቴ
የአዲስ ኪዳን ቁርባን መንበር ጠረጴዛ
ጽድቅን አሸተትን የሕይወትሽን መዓዛ /2/
ልቤ ተጠራጥሮ ኪዳንሽን ካልከዳ
ልመናም አልወርድም አልይዝም አኩፋዳ
ሁሉን እየሞላሽ መመገብ ታውቂያለሽ
ቢዝቁት የማያልቅ ጸጋና ሀብት አለሽ /2/
የእግዚአብሔር ማረፊያ ኮሬባዊት ዋሻ
የሕይወት ውሃ ምንጭ የህግ መፍሰሻ
ነበልባል ተዋህዶሽ ሙሴስ አንቺን አይቷል
ጫማውን አውልቆ በፊትሽ ተደፍቷል /2/
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.