ጠቅላላ

General

እዘምራለሁ

Lyrics

እዘምራለሁ ለእግዚአብሔር በፍፁም ደስታ

ላዳነኝ አምላክ ላቆመኝ ከሰዎች ተርታ /2/

እንዳለፈ ውሃ መከራዬን ያስረሳኝ እርሱ ነው

በእጆቹ ደግፎ ለምስጋና ያቆመኝ በጸጋው

መጽናናቴ እያልኩ የምጠራው ውለታው ማርኮኝ ነው

ፍቅሩ አስደነቀኝ ምህረቱ ለእኔ ያደረገው

ኃይልህ በድካሜ እንዲገለጥ ይህን አድርገሃል

ወጀቡን ገስጸህ ማዕበሉን እኔን አድነሃል

በጠላቴ ፊት በዘይቱ ራሴን ቀብቶኛል

ወደቀ ሲሉ ጠላቶቼ ሐይሌን አድሶታል

በሃጢያት ብረክስም በምህረቱ እኔን ጎብኝቶኛል

ፈፅሞ እንዳልጠፋ በመዳፉ በእጆቹ ቀርጾኛል

ተስፋ ያደረግኩት ምንም የለም ጌታ ካንተ በቀር

ወጥመዴን ስበር ሰንሰለቴን የሃጢያቴን ቀንበር

በሁሉ አንተ ጌታ እንደሆንክ አሁን አውቂያለሁ

ሐይልህ በድካሜ ተገለጠ ሁሉን አልፌአለሁ

ይሁን ያልከውን በሕይወቴ ፈፀምክ በፍቅርህ

ዳግመኛ በእጅህ ተሰራሁኝ በበጎ ፈቃድህ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening