✦
ጠቅላላ
•General
ሰረገላዎችህ
Lyrics
ሰረገላዎችህ የእሳት ናቸው
የሌጌዎን ጭፍሮች ማይችሏቸው
የገሐነም ደጆች ማይችሏቸው
አንተ ብቻ ቅዱስ ሐያል ጌታ
ሳመልክህ እኖራለሁ ጠዋት ማታ /2/
በእሳት ሰረገላ ታጥሯል መንገዳችን
ግያዝ ሆይ አትፍራ አለ ፈጣሪያችን
የጠላትን ምሽግ በቃሉ ይቆርጣል
ከእኛ ጋራ ያለው ከእነርሱ ይበልጣል
ከቴማን ተራራ ከፋራን ሲወርድ
ጠላት ይጨነቃል በድምጹ ሞገድ
ጦረኛ አያበዛም ሞአብን ሲመታ
በአህያ መንጋጋ ሺውን ጥሏል ጌታ
የጥልቁን መሠረት በነፋስ አስሮታል
ከሰማያት በላይ ዙፋኑን ዘርግቷል
ዘንባባ ይዛችሁ ግቡ ከመቅደሱ
በምስጋናው እሳት እንድትቀደሱ
ወደረኞቻችን ከቁጥር ቢበዙ
እንደ ቃየል ልጆች ሾተል አንመዝም
እንጀራ መግበን እንሰዳቸዋለን
በቀልና ፍርድን ለአምላካችን ትተን
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.