✦
ጠቅላላ
•General
ዛሬም አለሽ
Lyrics
ዛሬም አለሽ በልቤ /3/
ድንግል ሆይ ውለታሽ አይጠፋም ከሃሳቤ
እንደ ሃጢአቴ ብዛት እንደ በደሌማ
የጥልቁ ሰንሰለት ሲያንሰኝ ነው ጨለማ
ግን ያንቺ ሆንኩና ሁሉንም አለፍኩት
ያንን የሞት ባህር በምልጃሽ ቀዘፍኩት
አርፏል ልቤ ባንቺ ባዛኝቷ ማርያም
ውስጤ እየፈሰሰ ፍቅርና ሠላም
ህመሜን ቢያስረሳኝ የውዳሴሽ ቃና
እመቤቴ እላለሁ ዛሬም አንደ ገና
እናታችን ጽዮን ሰው ሁሉ ይልሻል
ዳዊት በበገና ያመሰግንሻል
የሐሴቦን ነገስታት ለክብርሽ ዘመሩ
የማትፈርሽው መቅደስ የእግዚአብሔር ሀገሩ
እጅግ ብዙ ነገር አድርገሽልኛል
ይቅር ባይም ልጅሽ በፍቅር አይቶኛል
እኔስ እኖራለሁ ድንግል ባንቺ ጥላ
ጨለማን አላይም ከእንግዲህ በኃላ
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.