✦
ጠቅላላ
•General
ያ ድሃ ተጣራ
Lyrics
ያ ድሃ ተጣራ እግዚአብሔርም ሰማው
ደርሶ ስላንኳኳ ከጸባኦት እንባው
አምላክ በቸርነት በምህረት ጎበኘው
ባለቀሰ ጊዜ ግራ የገባው ሰው
መሻትህ ብቻ ነው የሚፈለግብህ
እግዚአብሔርን ጥራ እመን ትድናለህ /2/
ንገረው ችግርህን የውስጥህን ብሶት
ይሽረዋልና አስፈሪውን ሕይወት
ግራ የተጋባው የተከፋው ገጽህ
ይበራል በጸሎት አምላክህን ጠርተህ
ለወገን ለዘመድ ያስቸገረው መላ
ሲቀል ታየዋለህ ካነባህ በኋላ
ሳግና ንዴትህ ይቀራል ይሻራል
በእርሱ ፈንታ ልብህ ሰላም ይሞላዋል
በከንቱ መጨነቅ እራስን መጥላቱ
ነውና የአጋንንት መግቢያ ምልክቱ
ሀዘን በህሊናህ በፈሰሰ ጊዜ
ንገረው ለአምላክህ የልብህን ትካዜ
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.