✦
ጠቅላላ
•General
ርሆቦት
Lyrics
ርሆቦት እያልን እንዘምር በእልልታ
ጌታ አብዝቶናል ውሎልናል ውለታ
የዝማሬ ነው የምስጋና ሰዓቱ
የእግዚአብሔር ልጆች ክንዳችሁን አበርቱ
ቃኝተነዋል በገና መሰንቆውን
ላናቋርጥ በፊቱ ምስጋናውን
በዕጣኑ ጢስ ታጅቧል ውዳሴያችን
ይሰማናል ያበዛል አምላካችን
ለአገልግሎት ስንወጣ ጥቂት ነበርን
በረሃውን ስንጓዝ በዛ ዘመን
ለመለምን በፍቅሩ እንደ ዋርካ
ለዚህ ቀን አስቦናል ጌታ ለካ
ሁሉም ሆኗል በጊዜው በፈቃዱ
እንቅፋቱም ተነስቷል ከመንገዱ
ያነሳሳን ያበረታናል ገና
ዓለምን እንከድናለን በምስጋና
ስናመሰግን ውለን እናድራለን
ያለድካም በፊቱ እንቆማለን
እንኳን በምድር በሰማይ በበጉ ፊት
ዝማሪያችን ይሰማል እንደ ዳዊት
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.