ጠቅላላ

General

ቸርነትህ ነው

Lyrics

ቸርነትህ ነው ያደረሰኝ እስከ ዛሬ

ቸርነትህ ነው የጠበቀኝ እስከ ዛሬ

ላመስግንህ የኔ ጌታ በዝማሬ /2/

መክሊቱን ቀብሬ ባሳዝንህ

መብራቴንም ይዤ ባልጠብቅህ

በታላቅ ይቅርታህ እንዳትረሳኝ

በፍቅርህ ጎብኝተህ ከሞት አውጣኝ

ከቤትህ እርቄ መች ጠገብኩኝ

በርሃብ በርዛት ተቸገርኩኝ

አምናለሁ አምላኬ እንድትምረኝ

ለይቅርታህ መጣሁ ተቀበለኝ

አንዳች እንደሌለኝ አውቀዋለሁ

ባንተ ቸርነት ግን እመካለሁ

የከበደው ሸክሜ ይቀለኛል

ይቅርታህ ለባሪያህ ይደርሰኛል

በመቅደስህ ቆሜ ለመዘመር

ስራህን ለትውልድ ለመመስከር

እኔ ማነኝ ብዬ አስባለሁ

አምላክ ቸርነትህን አደንቃለሁ

በሰው እጅ መመካት አቁሚያለሁ

እረዳቴ አንተ ነህ አውቂያለሁ

አንተ ከጠበቅከኝ በሕይወቴ

ቅጥሬ አይደፈርም መድሃኒቴ

የእኔን ስራ ተወው ተግባሬን

የመስቀሉን ነገር መርሳቴን

አዚሜን አንስተህ አንተን ልይህ

ኢየሱስ ክርስቶስ አምላኬ ነህ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening