✦
ጠቅላላ
•General
ሐረገወይን
Lyrics
ሐረገወይን ነሽ ድንግል የወልድ እናቱ
ብጽእት ይሉሻል እመአምላክ /2/ አንቺን ትውልድ ሁሉ
ስምሽ ልዩ ነው ለኛ ቤዛዊተ ኩሉ
የያዕቆብ መሰላል የሙሴ በትር
የእሳትን ባህር የምታሻግር
እመ ብዙሃን ናት የተሰጠች ለእኛ
ጥላ ከለላ ናት ከጥፋት መዳኛ /2/
ፍቅርና ሠላም የተገለጠባት
ሐረገ እግዚአብሔር ድንግል እመቤት ናት
የታጠረች ተክል የተዘጋች ደጃፍ
ለድንግል ምስጋና ይድረስ ከአጥናፍ አጥናፍ /2/
እጹብ ድንቅ ነገር ለእኛ ተሰጥቶናል
ሕይወት የምትለምን እናት አግኝተናል
እስከ ቀራንዮ ከጸና ጉዟችን
ድንግል ትገኛለች ያደራ እናታችን /2/
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.