✦
ጠቅላላ
•General
አስፈሪ ነበልባል
Lyrics
አስፈሪ ነበልባል ሁሉንም አልፌ
ይኸው በአምላኬ ቆምኩኝ ተደግፌ
ምስጋና አቀርባለሁ ሁሉን ቻይ ለሆነው
እንድዘምርለት ልቤን ለከፈተው
ለሰው ያልነገርኩት በውስጤ የቀረ
ያሳለፍኩት ስቃይ መከራ ነበረ
ወደ አንተ አልቅሼ ፈታህልኝ አምላክ
አይተህ ቸል አላልከኝ በባሪያህ አልጨከንክ
አምላክህ የት አለ ሲሉኝ ጠላቶቼ
አጥምደው ይዘውኝ እጃቸው ገብቼ
ሀዘን ነፍሴን ከቧት መድረሻ ጠፍቶኝ
ፈጥነህ ደረስክና ከሞት አዳንከኝ
ከእንግዲህ ወዲህ እኔ ተስፋ አልቆርጥም
ስራህን አይቼ ከቶ አልናወጥም
ወድቄ እንዳልቀር አስተምረኸኛል
ወጥመዱን ሰባብረህ ለዚህ አብቅተኸኛል
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.