✦
ጠቅላላ
•General
ስምህ በሁሉ ተመሰገነ
Lyrics
ስምህ በሁሉ ተመሰገነ
ከክብር በላይ ክብርህ ገነነ
አንተን ማወደስ ያስደስተናል
ስምህን ማክበር ግብራችን ሆኗል
አምላክ ተመስገን በሰማያት
ስምህ ይወደስ በፍጥረታት
ከህጻናት አፍ ምስጋና ይውጣ /2/
አንተን ማመስገን ይሁን የእኛ እጣ /2/
በምግብ እጦት ብንሰቃይም
ማህሌትህን አናቋርጥም
የመከራ ዶፍ ቢወርድብንም /2/
እንዘምራለን ለአምላካችን ስም /2/
ሰማዩ ዝናብ ደመና ቢያጣ
ፍቅርህ በእኛ ውስጥ አላቋረጠም
ቸርነትህን እንጠብቃለን /2/
ከአንተ ደጅ ጌታ የት እንሄዳለን /2/
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.