ጠቅላላ

General

ማርያም አርጋለች

Lyrics

ማርያም አርጋለች ወደ ገነት /4/

የሰማይ መላዕክት እያረጓጓት /2/

እሷም እንደ ልጅዋ ተነስታለች /2/

የአባትዋ ዳዊትን ትንቢት ልትፈፅም

ወርቁን ተጎናጽፋ በቀኙ ልትቆም

ወደ አምላክ ማደሪያ ወደ ሰማያት

አረገች በእልልታ ድንግል የእኛ እናት

አርጋለች ማርያም ተነስታለች

ሰማያት ይከፈት ደመናም ይዘርጋ

ዝምታም አይኖርም እመ አምላክ አርጋ

አንደበት ይከፈት ማርያምን ያመስግን

ከዘለዓለም ጥፋት በምልጃዋ እንድንድን

አርጋለች ማርያም ተነስታለች

የአምላክ ማደሪያ የ ቅዱስ ስጋሽ

አምላክን ያቀፉት እነዛ እጆችሽ

ሙስና መቃብር ይዞ አላስቀረሽም

ተነስተዋል በክብር በእምነት አየናቸው

አርጋለች ማርያም ተነስታለች

ሐዋርያት አበው እንኳን ደስ አላችሁ

በክብር አረገች ማርያም ሞገሳችሁ

ወደ ዓለምም ውጡ ስበኗን ይዛችሁ

የድንግል እርገቷን ንገሩ ተግታችሁ

አርጋለች ማርያም ተነስታለች

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening