ጠቅላላ

General

ማን አለን

Lyrics

ማን አለን ጌታ ሆይ ካንተ በቀር /2/

በሰማይ ሆነ በዚህ ምድር

ማን አለን ከአንተ በቀር

ዛሬ ወዳጅ ነገ ጠላት

ይለወጣል የሰው ሕይወት

ያመናቸው ገፍተው ጣሉን

አንተ ብቻ አትለየን

ሕይወታችን መልኩ ወይቦ

መንገዳችን በሾህ ተከቦ

ጠላት በዝቶ ስንሰቃይ

ታገልክልን ነህ ኤልሻዳይ

ባይደላንም የምድር ኑሮ

ብናሰማም ለቅሶና ሮሮ

ባይሳካ ውጥናችን

ባንተ ያምራል ፍጻሜያችን

እንኳን ጮኸን ሳንለምን

አፍሮ አይገባም ባዶ እጃችን

ስቦ ማውጣት እስኪያቅተን

በዓሳ ይመላል መረባችን

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening