ጠቅላላ

General

መላዕክቱ

Lyrics

መላዕክቱ በፊቱ ይቆማሉ

ሠራዊቱ በፊቱ ይሰግዳሉ

ሐያል አምላክ እግዚአብሔር እያሉ /2/

በክብረ መንግስቱ በነጭ ዙፋን ላይ

ዘለዓለም ይኖራል ከሰማያት በላይ

ለሚታዘዙለት እጁን ይዘረጋል

ጨለማውን በሰላም ያነጋል

መብረቅ ነጎድጓዱ የምስጋናው ጅረት

ዘወትር ይፈሳል በቀንና ሌሊት

የእሳት መጋረጃው ይነዳል ከፊቱ

ተቀኙለት ሊቀ መላዕክቱ

ትናንትናም ዛሬም እርሱ ህያው ነው

ሞትን አሸንፎ በአባቱ ቀኝ ያለው

ዳግመኛ ሲመጣ እርሱን ለመቀበል

በደመና እንነጠቃለን

በወርቅ ፅና ላይ ብዙ ዕጣን ጨምረው

ዙፋኑን ያጥናሉ በበጉ ፊት ቆመው

አዲሱን ምስጋና አዲሱን ውዳሴ

ያቀርባሉ ለቅድስት ስላሴ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening