✦
ጠቅላላ
•General
ገብርኤል
Lyrics
ገብርኤል /2/ ስለው ሰምቶ
መጣ ወደኔ ፈጥኖ
ሰንሰለቴን በጠሰው የአንበሶቹን አፍ ዘግቶ
ገብርኤል ስጋዬ ሳይረግፍ በአናብስቱ ጥፍር
ታድጎኛል ምልጃው የመልአኩ ክብር
በረሀብ ለነደዱ አናብስት ሲጥሉኝ
አንተ አለኸኝና ክንፎችህ ከለሉኝ
ገብርኤል ከአፎቱ ሲመዘዝ የጠላቴ ሰይፍ
አጽንቶ ይዞኛል ፍሬዬ ሳይረግፍ
አደገድጋለሁ አለኝና ፍቅሩ
በእሳት ክንፍ ታጥሯል የደጄ ድንበሩ
ገብርኤል በሰይፍ ተመትርዋል የክፉዎች ክህደት
ሐብሉ ተበጥሷል የአመጹ ሰንሰለት
ከቅዱሱ ድንጋይ ሕይወት የሚያፈልቀው
እንዳልለይ እረዳኝ ክብሬን ከፍ አደረገው
ገብርኤል አለው ልዩ ስልጣን ከአምላክ የተሰጠው
ይመጣል ወደ እኛ እሳቱን ሊያጠፋው
እኛም እናምናለን ሰምተናል አይተናል
የመላዕክት አለቃ ከአምላክ ያማልዳል
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.