✦
ጠቅላላ
•General
ሌላ ምስጋና
Lyrics
እመቤቴ ሆይ ሀብቴ ነሽና
ሳመሰግንሽ ዲያቢሎስ ቢቀና
ገና አለኝ ገና አዲስ ምስጋና
ገና አለኝ ላንቺ አዲስ ምስጋና
ድልድይ ሆነሽን ተሻግረናል እኛ
አንወሰድም አንሞትም ዳግመኛ
እናት አለችን በላይ በሰማይ
አማላጃችን እሙ ለአዶናይ
ግዮን ከቦታል የርስትሽን ሀገር
ጣፋጭ ተአምርሽ ይኖራል ሲነገር
ዋሻው ያበራል ሜዳው ሳር ቅጠሉ
መለኮሳቱ ንኢ ንኢ ሲሉ
ተፍገመገመ ራደ ጠላታችን
የልጅሽ ሞገስ ሰፍኖ በላያችን
ሞገዱም ይጩህ ዲያቢሎስም ያውራ
ከእሳቱ አንወድቅም ሳለን ካንቺ ጋራ
ቤትሽ አድገናል በአማረው እልፍኝሽ
የንጉሱ እናት እመ ብዙሃን ነሽ
የራማው መላዕክት ክንፎቹን ዘርግቷል
ወደ ገሊላ ምስጋና ተሰምቷል
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.