✦
ጠቅላላ
•General
አንተ ግን አንተ ነህ
Lyrics
አንተ ግን አንተ ነህ በፀባኦት ያለህ
ዘለዓለም የምትኖር ሁሉን አሳልፈህ
የሁሉ ባለቤት አንተ ግን አንተ ነህ
ደመናት ባይኖሩ ዝናብም ባይሰጡ
ጨረቃና ፀሐይ ብርሃን ባያወጡ
የፍጥረታት ፀባይ ሁሉም ቢቀያየር
አንተ ግን አንተ ነህ ህያው እግዚአብሔር
የምድር ሐያላን ትላንት የነበሩ
በጉልበት በስልጣን እጅግ የተፈሩ
ቦታውን ለቀዋል በጊዜአቸው አልፈው
አንተ ግን አንተ ነህ መንግስትህ ህያው ነው
ሁሉን ስትለውጥ የማትለወጥ
እንደየስራው የእጁን የምትሰጥ
ማለዳ ማለዳ አዲስ ነው ስምህ
ቀናት የመይቆጥሩት አንተ ብቻ ነህ
አመድ ሲሆኑ አየን የግሪክ አማልክት
በወርቅ እና በብር በእጅ የተሰሩት
ዘመን የማይሽርህ እንዲህ እነደዋዛ
አንተ ግን አንተ ነህ ፈጥረህ የምትገዛ
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.