✦
ጠቅላላ
•General
ዘንዶውን አሸንፏል
Lyrics
ሚካኤል ስለው ስሙን ስጠራ
የአምላኬ ብርሃን በላዬ በራ
አዛኝ ነው በእውነት ፍጹም አዛኝ
የሚጠብቀኝ የሚያጽናናኝ /2/
ከአለቆች ጋራ ህዝቡን የመራ
የሚመላለስ በእሳት ተራራ
ባህሩም ሸሸ ከማደሪያው
የጌታ መላዕክ ሲያናውጸው
ዘንዶውን አሸንፏል ስሙን በክብር ጽፏል /2/
ከባዱ ጋራ ሜዳ ሆኖኛል
የወህኒው መዝጊያ ተከፍቶልኛል
አልናወጥም ከቶም አልፈራ
የጌታ መላዕክ ነው ከእኔ ጋራ
ዘንዶውን አሸንፏል ስሙን በክብር ጽፏል /2/
ትዕቢተኛውን አሸንፎታል
ዲያብሎስ አሁን ዝናሩን ፈቷል
ታላቅ ጸጥታ በሠማይ ሆነ
እግዚአብሔር ብቻ ስሙ ገነነ
ዘንዶውን አሸንፏል ስሙን በክብር ጽፏል /2/
ሚካኤል ሲቆም ፈጥኖ ደራሹ
የሚቃወሙን አጥብቀው ሸሹ
ታላቁ መላዕክ ከፊት ቀደመ
ታሪክ ተሰራ እንባችን ቆመ
ዘንዶውን አሸንፏል ስሙን በክብር ጽፏል /2/
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.