✦
ጠቅላላ
•General
አንቺ የወይን ሐረግ
Lyrics
አንቺ የወይን ሐረግ ድንግል ልምላሜሽ የበዛ /2/
ምግብ ሆኖ /2/ ተሰጠን ፍሬሽ ለእኛ ቤዛ /2/
ባንቺ ሰማይነት ድንግል የወጣ ፀሐይ /2/
ብርሃን ነው /2/ ለጻድቃን ስሙም አዶናይ /2/
ፊደል ትመስያለሽ ድንግል ወንጌል ትወልጃለሽ /2/
ለመላዕክት /2/ የማይቻል ነበልባሉን የቻልሽ /2/
የመሶብ ምሳሌ ድንግል የኮከብ መገኛ /2/
በስጋችን በነፍሳችን እንዳንራብ አንቺ አለሽን ለእኛ/2/
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.