ጠቅላላ

General

ባለውለታዬ

Lyrics

ባለውለታዬ /2/ ከአመድ ያነሳኸኝ

ከትቢያ ተጥዬ ተመስገን ጌታዬ

በሩን ቢዘጋብኝ ስምኦን ጨክኖ

ዝቅ አድርጎ ቢያየኝ ከአይሁድ ጋር ሆኖ

እንድቀርብ ወደ እርሱ አዘዘ ጌታዬ

እግሩን አጥበዋለሁ ወድቄ በእንባዬ /2/

የቀራጭ አለቃ ቢሆንም ስራዬ

እንድወርድ ከዛፉ አዘዘ ጌታዬ

ማዕረጌን መሸከም እስኪያቅተኝ ድረስ

ቤቴ ተባረከ በኢየሱስ ክርስቶስ /2/

ድንጋይ የጨበጡ ፈራጆች ከበውኝ

ነውሬን ዘርዝረው ጌታ ፊት አቆሙኝ

ፈረደችባቸው ሃጢያትም በእነርሱ

በሰላም ሂጅ ብሎ ምሮኛል ንጉሱ /2/

የማምነውን አምላክ አውቀዋለሁ እኔ

በሰራልኝ ስራ በእድሜ በዘመኔ

ፍቅሩን ተሸክሟል የልቤ ትከሻ

ልለየው አልችልም እስከመጨሻ /2/

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening