ጠቅላላ

General

ድንግል በድንግልና

Lyrics

ድንግል በድንግልና ጸንሳ

በድንግልና ትወልዳለች

ስሙንም አማኑኤል ትለዋለች

ገና ሳይጸነስ ዘመኑ ሳይገባ

ገረድ መሆን ሻተች ትንቢቱን አንብባ

ልታያት ናፈቀች ያችን ቅድስት እናት

ለክብርዋ ተገዝታ ውሃ ልትቀዳለት

ባርያ ልሁን አለች ዝቅ አድርጋ ራሷን

መች አወቀችና እናቱ መሆኗን

ጥቂት ለሚሻ ሰው ያውቃል ብዙ መስጠት

በማህጸኗ መቅደስ ሲቀድስ ኖረበት

ሀር ወርቁን ስትፈትል በቤተ መቅደሱ

ማደርያው እንድትሆን መረጣት ንጉሱ

በህሊናው ተስላ የነበረች ምናብ

መሰላል ሆነችው ለአዳም ድህነት ርካብ

በጎ መዓዛዋን ውበቷን ወደደ

በማህፀኗ ሊያድር እግዚአብሔር ወረደ

ከኪሩቤል ይልቅ ጀርባዋ ተመቸው

ንጽህይት ናትና የማትቆረቁረው

የተዘጋጀ መቅደስ ከቶ እማትከፈት

ታትማ የኖረች የክብሩ ሰገነት

ማንም አይከፍታትም ጥበብ አላትና

የእስራኤል ቅዱስ ገብቶባታልና

በረቀቀ ጥበብ ድንግል ተደነቀች

በሆዷ ቅዳሴን እያስተናገደች

ጎንበስ አለች ማርያም ውዳሴ ልትሰማ

ከቅኔያት ሀገር ከሆዷ ከተማ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening