ጠቅላላ

General

ድንግል ፈጣሪዋን

Lyrics

ድንግል ፈጣሪዋን ወለደችው

በመጠቅለያም ጠቀለለችው

የለምና ስፍራ ለእንግዶች ማረፊያ

ግርግም አስተኛችው በከብቶች ማደሪያ

ጨነቃት ጠበባት የዳዊት ከተማ

የጌታ መወለድ ታምሩ ሲሰማ

ወረደ መልአኩ ምስራች ሊያወራ

የህጻኑም ክብር በምድር አበራ

ይህ ምስጢር ታላቅ ነው ከቶ ማይነገር /2/

ማርያምም በልቧ ትጠብቀው ነበር /2/

ሰባ ሰገል መጡ ከሩቅ ምስራቅ ሀገር

ወርቅ እጣን ከርቤውን ለእርሱ ለመገበር

በእናቱም እቅፍ አገኙት ህጻኑን

ለዓለም ተናገሩ ንጉስ መወለዱን

ይህ ምስጢር ታላቅ ነው ከቶ ማይነገር /2/

ማርያምም በልቧ ትጠብቀው ነበር /2/

የይሁዳ ምድር ምስጋና ተመላች

ንጉስ መጥቷልና ከናዝሬት ገሊላ

ታምሩን ትናገር ቤቴልሔም ታውራ

ዝማሬ ሲውጣት ተረስቶ ቆጠራ

ይህ ምስጢር ታላቅ ነው ከቶ ማይነገር /2/

ማርያምም በልቧ ትጠብቀው ነበር /2/

የማይታይ ታየ ተዳሰሰ እንደ ሰው

በጠባቡ ደረት አዳምን መሰለው

ገረማት ጥበቡ ታናሿን ሙሽራ

ተዋህዷልና ቃል ከስጋ ጋራ

ይህ ምስጢር ታላቅ ነው ከቶ ማይነገር /2/

ማርያምም በልቧ ትጠብቀው ነበር /2/

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening