ጠቅላላ

General

በሰማይ ለእግዚአብሔር ምስጋና

Lyrics

በሰማይ ለእግዚአብሔር ምስጋና

በምድርም ለሰው ልጅ ሰላም /2/

ተወልዷልና መድሃኒዓለም /2/

የሞቱ ዘመን ማብቂያው ሲቃረብ

መቋጫው ሲደርስ አስፈሪው ወጀብ

ከድንግል ማርያም ጌታ ተወለደ

የጠብ ግድግዳ በክንዱ ተናደ

ሰላም ታወጀ ነፃነት ሕይወት

ተወልዷልን የዓለም መድሃኒት

የሰማይ ዜማ ተሰማ በምድር

ባአፈ መላዕክት ለእግዚአብሔር

ቃሉን አልረሳም የምህረት ኪዳኑን

የማዳኑን ቃል ከአፉ የወጣውን

መሐላው ጽኑ ጸጸት የሌለበት

ላዳነን አምላክ እልል እንበልለት

አጽናኙን ድምጹን ሰማን በኤፍራታ

በዱር አየነው የፍጥረትን ጌታ

በሚቆምበር በሚያድርበት ስፍራ

እንሰግዳለን በጽዮን ተራራ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening