ጠቅላላ

General

እሰይ ተወለደ

Lyrics

እሰይ ተወለደ የዓለም መድሃኒት /3/

ይኸው ተወለደ የዓለም መድሃኒት /3/

በሶሪያ ታየ ፈጣሪ እንደ እንግዳ /3/

ብስራተ ልደቱን ለሁሉ ሲያስረዳ /3/

ትንቢት ተናገሩ ነብያቱ ሁሉ /3/

የእስራኤል ንጉስ ተወልዷል እያሉ /3/

ሰባ ሰገል መጡ ሊሰግዱ በሙሉ /3/

አምላክ ቀዳማዊ ተወልዷል እያሉ /3/

ሰባሰገል መጡ ይዘው እጅ መንሻ /3/

ወርቅ እጣን ከርቤውን ለማርያም እጅ መንሻ /3/

ህጻናት አደሩ ከልደቱ ቤት /3/

ውሃው ሆኗልና ማርና ወተት /3/

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening