✦
ጠቅላላ
•General
በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ
Lyrics
በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ /2/
የተባረከ ነው ቅዱስ /2/
ሠላምን የሚያውጅልን
ፍቅር አንድነትን የሚያጸናልን
እውነተኛ መካር የሆነ
ለህዝቦች ሠላም የቆመ
ከሞአብ ምድር የሚያወጣን
ከጠላት ወጥመድ የተቤዠን
የሕይወት እንጀራ የሆነው
በእግዚአብሔር ስም የመጣው
ለኢየሩሳሌም የሚያነባ
ቤተ መቅደስን የሚያጸና
ለተገፉት ሁሉ መጠጊያቸው
የመጽናናት አባት አለኝታቸው
አዕምሮን የሚያልፍ ሰላም ያለው
በጥዑም ቃሉ የሚያጽናናው
ነፍሴም እርሱን ወዳ ዘመረች
ሆሣዕና በአርያም እያለች
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.