ጠቅላላ

General

ምድረ ቀራንዮ

Lyrics

ምድረ ቀራንዮ ምድረ ጎለጎታ /2/

መድሃኒት ክርስቶስ በአንቺ ተንገላታ

የዓለም መድሃኒት በአንቺ ተንገላታ

መስክሪ አንቺ ምድር ጉኡዚቷ ስፍራ /2/

መድሃኒት ክርስቶስ ያየብሽ መከራ /2/

የእሾህ አክሊል ጉንጉን ደፍቶ በራሱ ላይ /2/

ደሙ እነደ ውሃ ሲፈስ በመስቀሉ ላይ /2/

እጅና እግሮቹ በችንካር ተመተው /2/

ይቅርታን አድርጎ ለዚያ ለሃጢያታቸው /2/

ሁሉን ማድረግ ሲችል ስልጣን ሲኖረው /2/

በቀራንዮ መስቀል ፍቅሩን ገለጸው /2/

መከራ በተራ ሲፈራረቁበት /2/

በደልም አልሰራም ምንም አይነት ስህተት /2/

ከሰማያት ወርዶ እንዲህ መዋረዱ /2/

የእኛን በደል ሃጢያት ክርስቶስ መወሰዱ /2/

ፀሐይ ከለከለች ለመስጠት ብርሃን /2/

ለመሸፈን ብላ የአምላኳን እርቃን /2/

በመስቀል ላይ ሆኖ ተጠማሁ እያለ /2/

ተገርፎ ተሰቅሎ ቀራንዮ ዋለ /2/

በቆረስከው ስጋ ባፈሰስከው ደም /2/

አቤቱ ተራዳን እስከ ዘለዓለም /2/

ቸሩ መድሃኒዓለም እባክህ ማረን /2/

ደካሞች ነንና ወድቀን እንዳንቀር

ደካሞች ነንና ጠፍተን እንዳንቀር

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening