ጠቅላላ

General

ወንበዴ ነበርኩኝ

Lyrics

ወንበዴ ነበርኩኝ ሀገር ያሰለቸው

በመስቀል ላይ ሆኖ ታሪኬን ለወጠው

አስበኝ ስላልኩት በኋላ ስትመጣ

ገነትን ለማየት የመጀመሪያ ሰው ሆንኩኝ ባለ ዕጣ

አቤት ፍቅሩ የእግዚአብሔር /2/

ግሩም ፍቅሩ የእግዚአብሔር /2/

ኃያል ፍቅሩ የእግዚአብሔር /2/

አስበኝ ስላልኩት አሰበኝ ጌታዬ

ወንበዴ ነበርኩኝ ስርቆት ነው ስራዬ

በመስቀል ላይ ሆኖ ህዝቡን ያስብ ነበር

እኔስ አላየሁም /2/ እንዲህ ያለ ፍቅር

አልታይም ብዬ ሃጢያትን ስሰራ

ተመለስ ይለኛል ስሜን እየጠራ

እንዳልሞትበት ነው በሃጢያት ታስሬ

ፍቅሩን አልዘልቀውም /2/ አንደዚህ ዘርዝሬ

መከራ ሲከበኝ መጥቶ ያጽናናኛል

በሀዘኔ ጊዜ እግዚአብሔርም ያዝናል

ዓይኑ ከእኔ አይርቅም ጥበቃው አይጠፋም

ስሙን እጠራለሁ /2/ በጌታዬ አላፍርም

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening