✦
ጠቅላላ
•General
ተወልዳለችና
Lyrics
ተወልዳለችና የጌታ እናት መድሃኒት /2/
እናመስግናት እናወድሳት እንውደዳት /2/
የአዳምን ሕይወት
አዳም ሲሰደድ ከጥንት ርስቱ
ፊቱን ሸፈነው ጭንቀት ፍርሃቱ
እያለቀሰ ገነትን ሲያጣ
ተስፋ አንቺ ሆንሽው የመዳኑ ዕጣ
ሊባኖስ ተራራ ተሰማ ዜና
ምስራቅ ወለዱ እያቄም ወሐና
ዳግማዊት ሔዋን ምክንያት ድህነት
ልደቷን ሰማን በቅድስት እለት
የልደትሽ ቀን ልደታችን ነው
በአንቺ ነውና ልጅ የተባልነው
ፉሪን የተባልሽ ቅድስት ተራራ
በአንቺ መወለድ ዓለሙ በራ
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.