ጠቅላላ

General

ስላሴን አመስግኑ

Lyrics

ሥላሴን አመስግኑ /2/

የምድር ፍጥረታት ዘምሩ እልል በሉ /2/

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ

ምስጋና ይገባል ከምንም በፊት

ዓለማትን ሁሉ ለፈጠረ ጌታ

ምስጋና ይገባል ከጧት እስከ ማታ

ኪሩቤል ሱራፌል የሚያመሰግኑህ

መላዕክት በሰማይ የሚዘምሩልህ

እኛም የአዳም ልጆች እንዘምራለን

በሰማይ በምድር እንጠረሃለን

ብራብ በስላሴ እጠግባለሁኝ

ብጠማም በአምላኬ እረካለሁኝ

ስላሴ አምባዬ ክብሬም ናቸውና

ሁሌም ይመሩኛል በሕይወት ጎዳና

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening