ጠቅላላ

General

ምስጋናዬን

Lyrics

ምስጋናዬን ለአምላኬ አቀርባለሁ

በማደሪያው ገብቼ እሰግድለታለሁ

ኤልሻዳይ ነው ጌታ ሁሉን ቻይ

ይፈጸማል አምናለሁ የልቤ ጉዳይ

ዘንባባዬን ይዤ እንደ ህጻንቱ

ሆሣዕና ልበለው ሰግጄ በፊቱ

ምንም ባዶ ብሆን እውቀት ቢጎድለኝ

ለስሙ ልዘምር ከልካይም የለኝ /2/

አምላኬ በፊትህ ቃል አለብኝ እኔ

ቋንቋዬ መዝሙር ነው ያንተ እንደ መሆኔ

በአሚናዳብ ደጃፍ በቅድመ ታቦቱ

ያ የክብርህ ኡደት ጠራኝ ማህሌቱ /2/

የሕይወት ትርጉሜ አንተ ነህ ደስታዬ

ስምህን ማገልገል ክብሬ ነው ስራዬ

ለታመነው ጌታ ምስክር የሆኑ

ከብረው ተመለሱ ለበረከት ሆኑ /2/

መነሻዬ አንተ ነህ ጉልበቴና ክብሬ

መድረሻዬም አንተ መደምደሚያ ቅጥሬ

በጽዮን ተራራ ስትገለጥ ያኔ

ነጩን ልብስ አልብሰህ አስለሳኝ ለቅኔ /2/

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening