✦
ጠቅላላ
•General
ምሕረቱ ለዘላለም ነውና
Lyrics
ምህረቱ ለዘለዓለም ነውና /2/
እግዚአብሔር ይመስገን /2/
ምህረቱ አይኖቼን ከእንባ ከሀዘን ታድጓል
ምህረቱ በዘመኔ ሁሉ መጽናናት ሆኖኛል
ምህረቱ ከቁጥርም በዝቷል ከአዕምሮም በላይ ነው
ምህረቱ ዘመን የማይሽረው ዘለዓለማዊ ነው
ምህረቱ ከነገስታት ማዕድ ዕድል ፈንታ ስጠኝ
ምህረቱ ከተረሳሁበት እኔን አስታወሰኝ
ምህረቱ ትንሽዋን ጸሎቴን ከትጋት ቆጥሮልኝ
ምህረቱ ከሰላሙ መንደር ከነዓን አገባኝ
ምህረቱ ይታደጋል ከሞት ከጥልቅ ለተጣሉ
ምህረቱ ምስራች ይሆናል በሞት ጥላ ላሉ
የሃጢያትን ክምር ከላያችን ንዶ
ደስታን ያለብሰናል ማቃችን ቀዶ
ለጠላት ዘለፋ እኛን መቼ ተወን
በደልን ደምስሶ ልጆቹ አደረገን
እስከ ሽበት ድረስ አስከ ሽምግልና
በዘመኔ ሁሉ ይረዳኛል ገና
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.